About

ዝክረ አቡነ መልከጼዴቅ ማን ነው

ዝክረ አቡነ መልከጼዴቅ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በአካል በነበሩበት ጊዜ የጀመሯቸውን መንፈሳዊ፣ ማዕበራዊ እና የልማት ሥራዎች የገንዘብ፣ የሙያ እና የሞራል ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት (ማኀበር) ነው፡፡ ማኀበሩ የብጹዕ አባታችንን የአገልግሎት ዘመን በቅርበት በሚያቁ ምዕመናን እና ካህናት አሳሳቢነት የሚያሳድጓቸው ሕጻናት እና መነኮሳት እንዳይበተኑ ፤ የጀመሩዋቸው አቢያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ተጠናክርው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ይረዳ ዘንድ ቋሚ የሆነ ገቢ ማግኘት የሚችሉ ሥራዎችን ለመደገፍ በዲያስጶራ የሚገኙ ምዕመናንን ለማስተባበር ኢትዮጵያ ካሉት ተቋማት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው እና በዲሲ እና ባሉ ….

ዝክረ አቡነ መልከጼዴቅ ሕጋዊ ሰውነት አለው

ማንኛውም በእርዳታ የሚሰበሰብ ገንዘብ ሕጋዊ በሆነ መልኩ ለሚመለከተው አካል እንዲያደርስ ሕጋዊ ሰውነት ይኖረው ዘንድ ዝክረ አቡነ መልከጼዴቅ በሚል ስያሜ በዲሲ የአሜሪካ ግዛት እውቅና ተሰጥቶት መንግስታዊ ያልሆ ድርጅት ተብሎ ተቋቁሟል፡፡ የራሱ የሆነ የታክስ መለያ ቁጥርና የባንክ አካውንት ከፍቷል፡፡ ኢትዮጵያ ያለውን ሥራ በቅርበት ለመከታተል እንዲያመች ገዳም ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ያለው ሲሆን የውክልና ደብዳቤም ተቀብሏል፡፡

ዝክረ አቡነ መልከጼዴቅ ምን ይሰራል

ማኀበሩ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥቶ ኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ለመደገፍ ገቢ ማስገኘት በሚቻልበት መልኩ እየሰራ ይገኛል፡፡ በአጭር ጊዜ እቅድ ለሌሎች ለፕሮጀክቶች ማስኬጂያ ይረዳ ዘንድ ተከራይቶ ገቢው ለሕጻናቱ ማሳደጊያ ፣ ለመነኮሳቱ ማገልገያ ይረዳ ዘንድ በብጹዕነታቸው ታቅዶ ሥራው ሊጠናቀቅ የመጨረሻ ውራ የቀረውን ለቡ ላይ የሚገኘውን ሕንፃ ማስፈጸሚያ የሚረዳ ገንዘብ ማሰባሰብ ፤ በረጅም ጊዜ በቋሚነት ሕጻናትን እና መነኮሳትን ስፓንሰር ማድረግ ለሚፈልጉ ምዕመናንን ማስተባበር፡፡