Biography

የከንባታ ሐድያ ጉራጌ እና ሥልጢ አኀጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከአባታቸው ከመምሬ ክንፈ ሚካኤል ወልደ ሰንበት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ ማርያም ወልደ መስቀል ግንቦት 25 ቀን 1952 ዓ.ም በምሁር ገዳም አካባቢ ተወለዱ፡፡ የአሁኑ አቡነ መልከ ጼዴቅ የዛን ጊዜው ሕጻን ኃይለ ኢየሱስ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ወደ ምሁር ገዳመ ኢየሱስ ገብተው ከፊደለ ሐዋሪያ እስከ ግብረ ዲቁና ያሉትን ትምህርቶች ከተማሩ በኋላ በ1962 ዓ.ማ በጊዜው የቤተ ክርስቲያናችን ፓትርያርክ ከነበሩት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ምሁር ገዳመ ኢየሱስን በጎነኙበት ወቅት ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ድቁና ተቀበሉ፡፡ የጀመሩትን መንፈሳዊ ትምህርት ጌዜ አግኝተው ለመማር እንዲችሉ ከወላጆቻቸው ቤት ተለይተው እዚያው ከሚገኘው ምሁር ገዳም ገብተው ገዳማዊውን ሥርዓት በወቅቱ ከነበሩት ከገዳሙ አስተዳዳሪ ከመምህር ገብረ ማርያም ወልደ ገሪማ ከአባው መነኮሳት በማጥናት የገዳሙ የዜማ መምህር ከነበሩት ከመምህር ፍሰሐ መንክር ጸዋትወ ዜማና አቋቋም ተምረዋል፡፡

በዚህ ወቅት በገዳሙ ውስጥ በረድእነት እንጨት በመስበር ውሃ በመቅዳት ቅዳሴ በመቀደስ በፍፁም ትህትና ገዳሙን አግልግለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እስከ 1970 ዓ.ም ድረስ በገዳመ ምሁር እና በአካባቢው በድቁና እየተዘዋወሩ ካገለገሉ በኃላ በ1971 ዓ.ም የዝዋይ ገዳም የመጀመሪያውን ዙር የሥልጠና እድል አግኝተው ወደ ዝዋይ አቀኑ፡፡ ዝዋይ ገዳም ከወረዱ በኋላ በጊዜው ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዬስ ካልዕ ስር ቁጭ ብለው በመማር በስብከተ ወንጌል መረብ ብዙ ምዕመናን የሚያጠምዱ የወንጌል ገበሬ ለመሆን በቁ፡፡ ብፁዕነታቸው መደበኛውን የዝዋይ ሥልጠና እንደፈፀሙ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዬስ ካልዕ መልካም ፈቃድ እዚያው ቀርተው ቀደም ሲል በነበራቸው መንፈሳዊ ዝንባሌ መሠረት በ1972 ዓ.ም ምንኩስናን እና ሥልጣነ ክህነትን ከብፁዕነታቸው ተቀብለዋል፡፡ በዝዋይ ገዳም በቆዩባቸው 8 ዓመታት ውስጥ የቅኔ ትምህርት መማሪያ ከአባ ማርቆስ ተፈራ (አሁን አቡነ ማርቆስ) ቀትሎም ከታዋቂው እና ዝነኛው መምህር ከንቡረ ዕድ ክፍለ ዮሐንስ መኮንን የተማሩ ሲሆን መዝገበ ቅዳሴ ከአባ ወ/ሚካኤል እና ከመምህር ኃይለ ማርያም ተምረዋል፡፡ በዚሁ ወቅት በገዳሙ ውስጥ በክፍል ካህናትን በማሠልጠን፣ ቅዳሴ በመቀደስ፣ ካህናቱን ለልማት በማሳተፍ ፣ በምግብ አዳራሽ ውስጥ መጽሐፈ መነኮሳትን በማንበብ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ገዳሙን አገልግለዋል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን በስብከተ ወንጌል ሐዋርያት በመሰማራት ሥጋና ነፍስን በሚያረካ ትምህርታቸው ብዙ ወጣቶችን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያናቸው መልሰዋል፡፡

በዚህ ዓይነት የአገልግሎትና የትምህርት ጊዜ በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ከቆዩ በኋላ በ1978 ዓ.ም ወደ ሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብተው ለ4 ዓመታት ያህል የሚሰጠውን የሥነ መለኮት ትምህርት ተከታትለው በ 1981 ዓ.ም ከብፁዕ ወቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን መደበኛ የሰንበት ትምህርት ቤት መምህር ሆነው አገልግለዋል፡፡ የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ከኮሌጅ እንደወጡ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ኃላፊ በመሆን አገልግሎታቸውን በሰፊው ጀምረዋል፡፡ በዚያ አጭር የአገልግሎት ቆይታቸውም በተለይም በናዝሬት ከተማ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት እንዲሁም በድሬደዋ ባሉ አቢያተ ክርስቲያናት እየተዘዋወሩ በማስተማር በጠለቀ በቃለ ወንጌል ትምህርታቸው ህዝቡን እያረሰረሱ በእውቀት ብርሃን ነፍሳቸውን በወንጌል እየማረኩ ሐዋርያነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ዓመት ጊዜ ሳይሞላቸው የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት ለከፍተኛ አገልግሎት ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ተላኩ፡፡ በዚያም በ1982 ዓ.ም ለዘጠኝ ወራት ያህል በቆዩበት ጊዜ በኢየሩሳሌም ካሉ የኢትዮጵያ ገዳማት አባቶች ጋር በአንድነት በመሆን ከሰጡት ሰፊ አገልግሎት እና ታዛዥነታቸው አንጻር በገዳሙ አባቶች ፈቃድ የቅዱስ ፊሊጶስ ገዳም ቄሰ ገበዝ በመሆንም አገልግለዋል፡፡ በሌሎችም አብያተ ክርስቲያነት መንፈሳዊ ተልእኮ ከማበርከታቸውም ጋር የሰንበት ትምህርት ቤት አቋቁመዋል ፤ እዚያው ሳሉ ‹‹ አሜሪካን እሰኩል›› በሚባለው የቋንቋ ት/ቤት እንግሊዘኛ ቋንቋ ተምረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ከኢየሩሳሌም እንደተመለሱ በ1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆነው ተመደቡ፡፡

የዚያን ጊዜው መልአከ ብርሃን አባ ኃይለ ኢየሱስ የዛሪው ብፁዕ አቢነ መልከ ጼዴቅ በስብከተ ወንጌል ምእመናን ለማገልግል በነበራቸው ሰፊ ምኞት ሁኔታው የበለጠ የተመቻቸላቸው በዚህ ጌዜ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ብፁዕነታቸው በአዲስ አበባ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል እየተባለ በሚጠራው ቤተክርስቲያን በቆዩባቸው ሦስት ዓመታት ሕዝቡን ጠዋት እና ማታ ከማስተማር በጠጨማሪ ብዙ ወጣቶችን በሰንበት ት/ቤት ኮርስ አዘጋጅተው በማሰልጠን ሰፊ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ከሰንበት ት/ቤት አባላት እና ከሰርክ የወንጌል ጉባኤ የተሻሉትን እና ላቅ ያሉትን ደግሞ ልዩ ስልጠና በመስጠት ለሰባኪያነ ወንጌል እንዲሁም ወደ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመላክ ለድቁና አብቅተዋል፡፡ በደብሩም ታላቅ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ እና ቢሮ የካህናት መኖሪያ ቤት በተጨማሪም ለሰበካው በመካነ መቃብርነት ያገለግል በነበረው ቦታ አዲስ የአቡነ ገብር መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያ አስተክለዋል፡፡

ከዚህ ሰፊ አገልግሎታቸው በኋላ በ1985 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ወደ መርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያ ተዘዋውረው ለአጭር ጊዜ ከአበለገሉ በኋላ በ1986 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ረዳት ቆሞስ ሆነው ሆሳዕና ላይ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በተላኩት መሠረት በዘመን ብዛት አርጅቶ የነበረውን የቤተ ክህነቱን ቢሮ በማደስ አዲስ ዘመናዊ ቢሮዎች እና አንድ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አሰርተው በቅዱስነታቸው ቡራኬ አስመርቀዋል፡፡ ብፁዕነታቸው ስብከተ ወንጌል የማስፋፋት እና ሕዝበ ክርስቲያንን የማስተባበር ፀጋ የተሰጣቸው ግብረ ገብ ሐዋርያ ስለነበሩ በዚህ ፀጋቸው በሆሳዕና ከፍተኛ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ ኀዳር 4 ቀን 1987 ዓ.ም የከምባታ ሐዲያ እና ጉራጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ተብለው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተሾሙ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከተሾሙበት ሀገረ ስብከት ደርበው የተለያዩ ኃላፊነቶችን እየተቀበሉ ቤተ ክርስቲያናቸውን የለ ዕረፍት አገልግለዋል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ በ1991 ዓ.ም በአውሮፓ የነበረውን ጊዜያዊ ችግር በትተው እና ሕዝቡን አስተምረው እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት እንግሊዝ ለንደን ላይ ማረፊያ በማድረግ ሰፊ አገልግሎት ሰጥተዋል፡፡ የስድስት ወር የአውሮፓ አገልግሎታቸውን በብቃት ተወጥተው ከተመለሱ በኋላ በሀገረ ስብከታቸው ላይ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከትን ደርበው ለአንድ ዓመት አገልግሎ ሰጥተዋል፡፡

ከዚህም በኋላ ከግንቦት በ1996 ዓ.ም እስከ ግንቦት 1999 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ቅድስት ቤተክርስቲያናቸው የጣለችባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ ተወጥተዋል፡፡ ከዚህም በመቀጠል በምሁር ኢየሱስ ገዳምና በአኀጉረ ስብከታቸው የተለያዩ ማህበራዊ ፣ መንፈሳዊ እና የልማት ሥራዎችን አከናውነዋል፡፡

His Grace Abune Melketsedek, Bishop of Kembata, Hadiya, Silte and Guraghe Diocese was born in 1960, on 1st June at Mehur, a rural place in the South-Central highland of Ethiopia. He lived his childhood with his father Kinfe Michael Wolde Senbet, a priest and his mother w/ro Askale Mariam Wolde Meskel, a house wife.

He began his early education at Mihur Eyesus Gedam, a famous monastery near his birth place. At the monastery he completed spiritual education from Ethiopian alphabet to Deaconry level. Engaging himself in fulltime at the monastery, he further enriched his spiritual knowledge by learning hymn and liturgies. Along with education he had served the monastery by collecting fuel wood, fetching water and liturgical services with complete politeness and loyalty. By joining the Ziway Hamere Berhan Saint Gebriel Monastery in 1978, he learned gospel and became zealous evangelist.

He was further ordained with monkery and priesthood with blessings in the hands of His Grace Abune Gorgorios II, head of the monastery. During his eight years-stay in the monastery, he had acquired more knowledge in the fields of prose & verses as well as various liturgical services from different church fathers and authorities. Latter on, he was promoted to train priests in liturgy and assign them on development activities. Moreover, participating actively in apostolic missions that quench body and soul, he has brought back many youth souls to the holly church.

In pursuit of spiritual wisdom he joined the “Sewaswe Berhan Kidus Paulos” Higher TheoTheological College in 1985. While attending the Four-year course, he has served as a Sunday school teacher at “Debre Selam Kidus Stefanos” Church. After his graduation from the college and received a diploma from the hands of His Holiness Abune Merkorewos, he was appointed as head of Evangelical Department at East-Shewa Diocese and worked there for about a year.

By the order of the Holly Synod, he was again assigned to a greater service at holly Jerusalem. In witnessing his faithfulness and loyalty, the fathers of the monastery appointed him as head of the Saint Philipos Monastery. Along side with his duties he had learned English language at American School.

Upon his return from Jerusalem, he was appointed as an Administrator of “Debre Bisrat Kidus Gebriel” Church in Addis Ababa. In addition to those mentioned, the following positions are where he had worked on.

  • Administrator, “Debre Hail Kidus Raguel” Church.
  • Assistant to Bishop of East-Shewa Diocese.
  • Archbishop, East-Shewa Diocese.
  • Head of the Delegation of Ethiopian Orthodox Church to Europe.
  • West-Shewa Diocese was included to his leadership.
  • Manager of the Ethiopian Orthodox Church from May 2004 to May 2007.
  • Continued on working Archbishop’s position until the date of his death on 21st June 2010.

From spirituality point of view, His Grace Abune Melketsedek was a devoted and committed person in preaching, in helping the poor, in building churches and expanding worship services. He was also zealous on religious matters. He had produced many disciples.